በምንጮቻችን መረጃ መሰረት እነኝህ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በተጠቀሰው
ቀን ማታ ከ12 እስከ ሦስት ሰአት ምሽት የህወሓት ካድሬዎች በዝግ አዳራሽ ሰብሰበው፤ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የትግራይ ብሄር
ተወላጅ በከፍተኛ አመራር ካልሆነ በስተቀር በታችኛው የሰራዊት አባል ግን የትግራይ ብሄር ተወላጅ የሚባል ስለሌለ ለዚህ ደግሞ እናንተ
ልትሸፍኑት ይገባቸኋል በማለት፤ የትምህርት ቤቱ ዳሬክተር ከሌሎች የስርአቱ ካድሬዎች ጋር በመሆን በከፍተኛ ሁኔታ ቅስቀሳ እንዳደረጉላቸው
ለማወቅ ተችሏል፣
በተመሳሳይም በሃገር ደረጃ 10ኛ ና 12ኛ
የጨረሱ ተማሪዎች ወደ ውትድርና እንዲገቡ የገዢው ስርአት ካድሬዎች በልዩ ቅስቀሳ ተጠምደው እንዳሉም መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣