Wednesday, September 2, 2015

በሰሜን ሸዋ ዞን፤ መራኛ ወረዳ የሚገኝ መምህር ጌታቸው የተባለ አስተማሪ ብሶትህን በጀርመን ሬድዮ ጣቢያ የአማርኛ ፕሮግራም በኩል አስተላልፈሃል በሚል መታሰሩን ተገለፀ።






    በደረሰን መረጃ መሰረት ሰኔ 2007 ዓ/ም ላይ ላይ በአገሪቱ ውስጥ የሌለውን ችግር አለ ብለህ አስተላልፈሃል በሚል ምክንያት ነሃሴ 4/2007 ዓ/ም ከመኖርያ ቤቱ ተወስዶ መታሰሩ ታወቀ።
    የሰሜን ሽዋ ዞን፤ መረኛ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ህብረተሰብ ግለሰቡ ለምን ይታሰራል በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግም ሰሚ አካል እንዳላገኘ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።