እንደ
ታዛቢዎች ገለጻ ኢሕአዴግ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየሰራ ያለው ፕሮፓጋንዳ ኪሳራ እንደሆነ ካድሬዎቹ እየተናገሩ ሲሆን ካድሬዎቹ
ድርጅታቸው የሚሰራው ዶክመንተሪ ፊልም አሊያም ቃለመጠይቅ እንዲሁም ሃተታና መግለጫ በሕዝቡ በተቃራኒው እንደሚተረጎም ተቀባይነት እንዳሌለውና ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሚሰራው ስራም ውስጥ ውስጡን እየገዘገዘው መሆኑን እንዲሁም በቅርቡ የተከሰተው የትህዴኑ ሊቀመንበር ሞላ አስገዶም የውሸት ፕሮፓጋንዳ ኢሕአዴግን ጎዶሎ አድርጎታል ሲሉ ፕሮፖጋንዳው ኪሳራ እያጋጠመው መሆኑን ተናግረዋል፣
ታዛቢዎቹ ጨምረውም ዝምታን በተመለከተ የተናገሩት ካድሬዎች ድንገት ከህዝቡ
መሃል የሚፈነዳ ችግር እንዳይኖር በሚል በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች ተከፋፍለው መነጋገራቸውን ሲገልጹ ምርጫ 2007
በተመለክተ ድርጅታቸው 100% የፓርላማ ወንበር አሸነፈ እንጂ የሕዝቡን ድርሻ አላካተተም የሕዝቡን ልብም አላሸነፈም ሲሉ
በተዘዋዋሪ ምርጫውን እንዳጭበረበሩ ማመላከታቸውን ገልፀዋል፣