Saturday, April 18, 2015

ከፍተኛ የኢህአዴግ መሪዎች በደቡብ ክልል ጋምጎፋ ዞን፤ በሄዱበት ጊዜ። በአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ እያጋጠማቸው እንዳሉ ምንጮቻችን ከአካባቢው ገለፁ፣



በመረጃው መሰረት። የጋሞጎፋ ዞን ህዝብ ከመጋቢት 21/ 2007 ዓ/ም ጀምሮ እያካሄደው ያለው። በስርአቱ ላይ ያነጣጠረ ተቃውሞ ያሰጋቸው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች። በአካባቢው የሚገኙ የታጠቁ ሚልሻዎችንና  አባሎችን ከህዝቡ ጋር እንዳይወግኑ በመፍራት ለእያንዳንዳቸው ከ500 እስከ 1600ብር እየሰጧቸው  እንደሚገኙና። ይህንን የታዘቡ ነዋሪዎችም “ከኢህአዴግ ስርአት ከማጭበርበርና ከማደናገር  በስተቀር። ያገኘነው ጥቅም የለም ስለዚህ የስርአቱን  መለወጥ እየፈለግን ነው ያለን” በማለት ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ እንዳሉ ታወቀ፣
    መረጃው ጨምሮ።  የደህዴን/ኢህአዴግ ጉጅሌ ባለስልጣናት እያጋጠማቸው ያለው ተቃውሞ በጋሞጎፋ ህዝብ ብቻ ሳይሆን። በሁሉም የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዘንድ እያጋጠማቸው ያለ የጥላቻ ተቃውሞ እንደሆነ ሊታወቅ ተችሏል፣