በምጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች
ኣንዲሁም ቀበሌዎች የሚገኙ የሕወሓት ካዴሪዎች ወጣቶች አገራቸውን ትተው ወደ ውጭ እንዲያመሩ አጥብቀው እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጸው
መረጃው የዚህ ምክንያት ደግሞ በገጠር የሚኖሩ ለአቅመ አደም የደረሱ ወጣቶች ለእርሻ የሚሆን መሬት እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው የተነሳ
እንዲሁም በከተማ አካባቢ የሚኖሩ ወጣትች ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኃላ ስራ አጥተው ስለሚጎሳቆሉ በዚህም የተነሳ ሰርተው የሚኖሩበት
እድል እንዲመቻችላቸው በተደጋጋሚ በመጠየቅ ስለ ሚያስቸግራቸዉ ከዚህ የተነሳ ካድሬዎቹ ወጣቶችን ከአገር እንዲወጡላቸው አበክረው
እየሰሩለት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በተለይ ደግሞ በትግራይ ማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ የሚገኙ አስተዳደሮችና
ካድሬዎች ከቀበሌ አስተዳደር ጋር በመሆን ወጣቶችን ከፊታቸው ገለል እንዲሉላቸው በማለት ይህንን እኩይ ተግባራቸው በሰፊው እየሰሩለት
እንደሚገኙና በወረዳው የሚገኙ ቀበሌዎች ሰምሃል፤ ማይ ሓማቶና ገርሁ ሰርናይ ከሚገኙ አካባቢዎች ከራምዲ፤ ማይ ሃማቶ፤ ሌቶ፤ እንዳ
ልዕለይ፤ ከለሊዕ፤ ማይ ኩሩምቶ፤ እንዳርጋብ፤ እምባ ጅላይ፤ እምፋራ፤ ምእራይ ኩህሊ፤ ውንጡሕ፤ ደቀ'ሎም፤ ሕልብሎ፤ ሕጻ ጉዛና
ሌሎች አካባቢዎች በገዢው ስርአት ኔትዎርክ አማካኝነት በማድረግ የሚደረግላቸው ቅስቀሳዎች በመደናገር ቀን በቀን ያለመቃረጥ ተደራጅተው
የሚወዷትን አገር ጥለው ለህይወታቸው ዋስትና ወደ ማይሰጠው በርሃንና ባህርን አቆራርጠው ስዉዲ
ዓረብና አውሮፓ ሃገራት ለመሻገር ሲሞክሩ ህይወታቸው እንደሚያጡ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
የገዢው ህወሓት ኢህአዴግ መሪዎች በበተለያዩ
የሚዲያ አውታሮችና መድረኮች በመቅረብ ሰደት አማራጭ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ መልካቸውና ቃላቶቻቸውን በመቀያየር የሚናገሩት ውስጣቸውን
ለማያውቅ ሰው ለማደናገር እንደሆነ መረጃው በመጨረሻ ዘገባው አገንዝቧል።