Sunday, March 8, 2015

ገዥው የኢህ.አ.ዴ.ግ ቡድን እውቅና ያላቸውን አንዳንድ ተቃዋሚዎችን አድራሻቸውን በማጥፋት ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ከተለያዩ የአገራችን አከባቢዎች አስውቋል።



እንደምንጮቻችን ዘገባ ከ1997 እስከ 2002 ዓ/ም መጨረሻ  በፌዴራል ተወካዮች ምክር ቤት ተቀማጭ የነበረውን አቶ ጥላሁን አበበን የካቲት 8 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት ይኖርበት ከነበረው ምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ፈረስ ቤት ከተባለ ከተማ ታፍኖ እንደተወሰደ የገለፀው መረጃው ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ እስካሁን የት እንደሚገኝ ባለማወቃቸው ምክንያት ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባው አንተነህና ለድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ለአቶ አምደወርቅ ልየው  በተደጋጋሚ የት እንዳደረሳችሁት ንገሩን በሚል ቢጠይቋቸውም እስካሁን ምንም ምላሽ እንዳላገኙ ለማወቅ ተችሏል።
   በመጨረሻም የፌድራል ተወካዮች የምክር ቤት አባል የነበረው አቶ ጥላሁን መጪውን ምርጫ ለማደናቀፍ ከ6 በላይ ወጣቶችን  ጫካ ውስጥ አስገብቶ እያሰለጠነ ነው በሚል የሃሰት ውንጀላ እንደታሰረ የደረሰን መረጃው አክሎ አስታውቋል።