በመረጃው መሰረት በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ቁጥጥር ስር የሚገኙት
ወታደሮች። የሚከዳና የሚሞት እንዲሁም አታስፈልግም ተብለው እየተባረረ ያለው የሰራዊት ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ
ምክንያት ክፍለ ጦሮችንና ረጅሜንቶች ከነበሩበት የሰው ሃይል እጅግ
ተቀንሰው እንዳሉ የገለፀው መረጃው እነዚህ የእለት ጉርሻቸው ሲሉ ወደ መከላከያ ሰራዊት ተቀላቅለው በሁሉም ዳር ድንበሮችና ጎረቤት
ሃገር ሶማሊያ በየጊዜው ያለ ማቛረጥ በተካሄዱት ወጊያዎች እስከ ውስጥ ገብተው እንደ ቅጠል እየረገፉ ሰላለቁ በተጨማሪም በብዛት
በመክዳታቸው የተነሳ ከታች የቲም አባላት ጀምሮ እስከ እዞች የሚገኙ የሰራዊቱ መዋቅር በሰው ሃይልና በአካላዊ ብቃት በከፍተኛ ሁኔታ
ተጎሳቑሎ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ሰለሆነም ብዛት ያላቸው ሰራዊት የያዙት ክፍለ ጦሮችና ረጅሜቶች በማፍረስ
በተነፃጻሪ የተሻለ ሰራዊት ያላቸው ክፍለ ጦሮችና ረጅሜቶች የሰው ሃይል በማምጣትና በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ መረጃው አስረድቷል።
ከዚህ በፊት በአብዛኛዎቹ ረጅሜንቶች እያንዳንዳቸው
የነበራቸው የሰው ሃይል ከ650-700 የሚጠጋ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን ከዚህ በታች የሰው ሃይል ያላቸው ረጅሜንቶች በማፍረስ በተደረገው
የማስተካከል እርምጃ ከ1100-1300 ወታደሮች እንዲይዙ ተደርጎ ይገኛል።