በስራ ማጣት ምክንያት ማህበራዊ ኑሮአቸውን ሊመሩ ስላልቻሉ
317 ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ደቡብ አፋሪካ ለሰደት በሚሄዱበት ጊዜ በማሊ ፖሊሶች ተይዘው እሰር ቤት ተዘግተው እንዳሉ የገለጠዉ መረጃዉ የአገሩ ፍርድ ቤት
የወሰነላቸው የገንዘብ የእስራትና ቅጣት ቢጨርሱም የሚከታተልላቸው የህግ ጠበቃ የሚሆንላቸዉ አካል ባለማግኘታቸው የተነሳ እስከ
አሁን ድረስ በእስር ቤቱ ውስጥ ታጉረው ለተለያዩ በሽታዎችና ሞት አደጋ እየተጋለጡ መሆናቸው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተባለው
የዜና ወኪል ጥቅምት 3 2008 ዓ/ም ዘግበዋል።
የኢህአደግ ስረአት ባለስልጣናት ሃገሪቱ አድጋለች፤ ሰላምና
መልካም አስተዳደር ሰፍኖዋል በማለት በሚድያዎቻቸው እየገልፁ ባሉበት ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደ ስደት እየፈለሱ
ለሰቃይና ለሞት አደጋ እየተዳረጉ ያለ መሆኑን ደርጅቱ ጨምሮ
317 ሰደተኞች ከማላዊ አገር ወደ አገራቸው ለመመለስ 200 ሺ ዶላር እንዲሚያ ስፈልጋቸው ቢታወቅም ለነዚህ
ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚያሰብላቸው አካል ባለመኖሩ የተነሳ በአገረ ማላዊ የሚኖሩ የተለያዩ የገል ድርጅት ወኪሎች የሆኑትና
ዲፕሎማት መሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎቹ የማያሰብ መሆኑን አመልክተዋል፣፣