መረጃዎቻችን እንደገለፁት በማእከላዊ ዞን መረብ
ለኸ ወረዳ
በምሕቛን ቀበሌ ዓዲ ወይቦን እንኮ ኳናን አካባቢ በ1972
ዓ/ም ተከፋፍሎ የተሰጠ የእርሻ መሬት ሲሆን የዚህ አከባቢ ነዋሪ ህዝብም እስከ አሁን ድረስ ያለ ምንም ጭቅጭቅና ጥላቻ ሲጠቀምበት የቆየ ሲሆን። ካለፈው ሶስት ሁለት አመታት ጀምሮ ግን በሁለቱም
መንደሮች በመሬት ይገባኛል በሚል ጥያቄ ነዋሪዎቹ በከባድ ግጭት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ታወቀ።
በመረጃው መሰረት ከ30 ዓመታት በፊት ጀምረው መንደሮቹ የመለያያ ዳርቻቸው አውቀው በሰላም የቆዩ ሲሆኑ አሁን ግን የመሬት
ይገባኛል ጥያቄ ሊያነሱ የተገደዱበት ዋናው ምክንያት። የአካባቢው
አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች በሚከተሉት ህዝብ ከህዝብ ጋር የማጋጨት አሰራርና ተንኮል መሆናኑንና ከዚህ ተነስተውም የዓዲ ወይባ መንደር ሲጠቀሙበት የቆየ የእርሻ መሬት በዳርቻው
የምትገኝ የእንኮ ዃና ነዋሪዎች ቦታው ለእኛ ነው የሚገባው ብለው
ጥያቄ ባነሱበት ወቅት። የወረዳውና የቀበሌው አስተዳዳሪች ግን አስታራቂዎች መሰለው በመቅረብ የሁለቱም መንደር ነዋሪዎች የሚያጣላ አስተያየት በሚያቀርቡበት ግዜ ነዋሪዎቹ ስለ ነቁበትና ተቀይባነት ሰላጡ የእርሻ መሬቱ ተከልሎ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ማድረጋቸወን
መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።