Wednesday, November 11, 2015

በወርዒ-ለኸ ወረዳ የሚገኙ ወጣቶች ለማህበር እየተባለ የሚከፍሉትን ገንዘብ ህጋዊ መቀበያ ወረቀት ስለ ማይሰጣቸዉ በድጋሚ ለመክፈል እየተገደዱ መሆናቸዉ ታወቀ።



በመረጃዉ መሰረት በማእከላዊ ዞን ወርዒ ለኸ ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የወጣቶች ማሕበር ያልከፈለ ወጣት የተራራ መሬት በሚደረግ ክፍፍል መቢቱ አይጠበቅለትን እያሉ በመስፋራት የሚወስዱት ገንዘብ ያለ ህጋዊ መቀበያ ወረቀት በመሆኑ በተነሳ ወጣቶቹ አልከፈላቹም እየተባሉ በድጋሜ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ባሉበት ወቅት የከፈሉት ገንዘብ ቢሆንም በምን እንደሚዉል አይታወቅም ሲሉ እነኝህ ወጣቶች በምሬት ገለፁ።
እነዚህ አስተዳዳሪዎች የሚከተሉት የተራራ መሬት አሰጣጥት ፍትሃዊነት የጎደለዉ፤ በቀደሚያ የሚሰጣቸው የገዢ ስርኣቱ አባላትና ዘመድ ወገን ያለዉ በመሆኑ በአብዛኛዉ ወጣቱ ግን ያለሆነ ምክንያት እየፈጠሩ ስለ ማይሰጡት ወጣቱ እግሩ ወደ አመራበት መሰደድና እንዲሁም ወደ ከተማ መፈለስ እንደ ዋነኛ አማራጭ አድርገዉ እንደሚወስደዉ መረጃ አክሎዉ አመለከተ።