Monday, November 2, 2015

ፍየሎች ቢመካከሩ አቛማቸው አንታረድ!!



እንደሚታወቀው ኢህአዴግ እሱን የሚመራው ገዢ ስርአት ጉባኤዎች ለማካሄድ በሚል እንደ ደንብ ያስቀመጠው ተከትሎ አስር ዙር ያሚህሉ  ጉባኤ አካሄዶ ይገኛል: በኢህአዴግ ስር ሆነው በግባር ደረጃ ያሉት እንደ ሕወሃት፤ ብአዴን፤ ኦሆዴድና ደኢህዴን የተባሉት ድርጅቶች ቀድሞውም ለይስሙላ ጉባኤ አካሂደናል ለማለት ከላይ በፌደራል ደረጃ በስርአቱ የሚገኙ እያንዳንዳቸው የክልል መስተዳድሮች ወርደው በነሃሴ ወር ያካሄዱትን ጉባኤዎች ሲታይ የስብሰባው አፈፃፀም በአገራችን በመልካም አስተዳደር ምክንያት በህዝቡ ማህል ተከስቶ ያለው መጠራጠርና ጭቁኑ ህዝብ እያሳለፈው ያለውን የኖሮ ሁኔታ። እንዲሁም የኖሮ ደርጃው ከብዶት በርሃብ አለንጋ እየተገረፈና ፈትህ በማጣቱ መክንያት ወደ  ስደት በሚያመራበት ጊዜ በተለያዩ አገሮች በመታሰርና በመታረድ ላይ ያለው ዜጋ በሚመለከት። በደንብ ታስቦበትና ተወያይቶበት መነሻውና መፍትሄው እንደ ድርጅትና መንግስት ውሳኔዎችን ያሳረፉለት ሳይሆን። በደፈናው አገራችን በኢህኣዴግ አማካኝነት ለከፍተኛ የእድገት ደረጃ ደርሰች፥ በየአመቱ ባለ ሁለት አሃዝ እድገት አስመዘገበች፥ ያቀድ ነው 1ኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን በድል ተጠናቀቀ፥ 2ኛ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በከፍተኛ ደረጃ ይቀጥላል በሚልና ሌሎች መግለጫዎችና ቃል እየደሰኮሩ የኢትዮጵያን ህዝብ እያላገጡበት መሆናቸው ሁሉም ዜጋ ሊያውቀው ይገባል።
ጉባኤው ግን ሁሉ ጊዜ እንደሚያደርጉት ስልታዊ በሆነ መድረክ እየተመራ አናሳዎች በሚያሽከረክሩት እንዲመራ በማድረግና በጉባኤተኞች የህልውና ጥያቄ ቢቀርብም እንኳ በየሴክተሩ ሃላፊዎችና የክልል አስተዳደሮች  የተሰጠው መልስ ግን  ያሚያሰልች፤ አስመሳይና አደናጋሪ አካሄድ ሆኖ እንዳለፈ የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም ጉባኤው ከጅምሩም የተጨረሰ ስለ ሆነ እንደ ግዴታ የተወሰነ ህዝብ አሳትፈው እይሉንና ስሙሉን ተብሎ መፈፀም ስለ ሚገባው በጉባኤው የተሳተፈና በሚድያዎች የተከታተለ ህዝብ ግን መጥፎ ትምህርት ሆኖበት ያለፈ ነው።
በዚህ መሰረት ደግሞ በተሳታፊዉ አብዛኛው ድምፅ ያገኙ መሪዎች  እያሉ ዝቅተኛ ድምፅ የገኙት በአመራርነት በነበሩበት ቦታ እንዲቀጥሉ በማድረግ። ሌሎች ነባር አመራሮች ደግሞ እድሜን መሰረት በማድረግ ተብለው የተወሰኑ የወጡ'ኳ ቢሆኑም የስልጣን ጥማት መነሻ በሆነው ይዘዉት የነበሩት ስልጣን ላለማስረከብ እርሰ በራሳቸው መጎጃጀልና አምሳያህን መፈለግ እንዳስከተለ የታወቀ ነው።
ባጠቃላይ የኢህአዴግ መሪዎች በላፈው ወር ያካሄዱት ጉባኤዎች አስከትለው በወርሃ መስከረም በአቅራቢነት የጉጅሌው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተደረገው የካብኔ ሚንስትሮች ሽመት የህዝብ ውክልና በሌለው የይስሙላ ፓርላማ እንዲፀድቅ የተደረገው ድራማ ለውጥ የታየበት ሳይሆን ልክ እንደበፊቱ የፖለቲካ አስተሳሰብ መለኪያ መሰረት ያደረገ ሽመት በነበሩበት እንዲቀጥሉ ሲደረጉ በአንዳንድ የሴክተር መስራቤቶች የተደረገው ለውጥና መስፋፋት ቀጣይነት ያለው ሳይሆን  በየጊዜው ፈርሶ የሚቀያየር ማደናገሪያ የስርአቱ አካሄድ መሆኑን ሁሉም የሚያወቀው ሃቅ ነው።
ስለ ሆነም የህዝብን ጥቅም በተዳፈንበትና በሳል አምራር ሰይወጣ ለቡድናዊ ጥቅማቸው ሲሉ “ፍየሎች ቢመካከሩ አቛማቸው አንታረድ" እንደሚባለው ለግል ኑሯቸው ብቻ በማትኮር የህዝቡን ጥያቄና ተስፋ ገሸሸ እያደረጉት ሲሆኑ ውጤቱ ግን ሁሉ ጊዜ እንቅልፍ እየነሳቸውና እየፈሩለት ያለ በሽታ 'ውን ሆኖባቸው ያለ ከክሰረት እንደማያመልጡና መጨረሻውም አገርና ህዝብ ይዘው ወደ ውድቀት በማምራት ላይ ይገኛሉ።