ልዑል ገ/ማርያም የተባለ የኢህአዴግ ስርዓት ዳኛ ከስራው ከጠፋ ስምንት ወር ያስቆጠረ ሲሆን እስካሁን ድረስ የት እንዳለ እንደማይታወቅ ያገኘነው መረጃ
አስረድቷል።
ከፍተኛ
ዳኛው ዕድሜው 57 መሆኑን የገለፀው መረጃው፥በኢህአዴግ ስርዓት ፓርላማ በጤና ጉድለት እና ዕድሜ መግፋት ምክንያት ሊሰራ ስላልቻለ
የጡረታ መብቱ ተክብሮለት ከግንቦት 1 2009 ዓ/ም ጀምሮ ከስራው እንዲሰናበት የሚል ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር ይታወቃል።
ባለስልጣኑ
አንድ ግዜ ወደ ኖርወይ በሌላ ግዜ ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለህክምና ሄዷል የሚል መረጃ ቢኖርም፣ ለተከታታይ ስምንት ወራት ስራው ላይ እንዳልተገኘ
ለማወቅ ተችሏል።
የተሰወረው
ዳኛ በበሽታ ይሁን አይሁን እስካሁን የታወቀ ነገር እንደሌለና ባለቤቱን ጨምሮ መላው ቤተሰቡ የት እንዳለ እስካሁን አለማወቃቸው አነጋጋሪ
ጉዳይ ሆኖ እንዳለ እየተገለፀ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዳኛው ምናልባት ከስርዓቱ
ጋር አለመግባባቱን ተከትሎ በድብቅ ሳይገድል አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳለ መረጃው ጨምሮ
አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment