Sunday, April 12, 2015

በደቡብ ወሎ፤ ጃማ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ የኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች። እያወረዱት ባለው ከፍተኛ ግፍ የተማረረው ህዝብ። በላያቸው ላይ የግድያ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተገለጸ፣



በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፤ ጃማ ወረዳ፤ ኤልሻል በተባለው ቀበሌ ውስጥ ሊቀመንበር ሆኖ ህዝቡን ሲበድል የቆየው ዘለቀ ፀጋየ የተባለውን የስርአቱ ካድሬ። መጋቢት 19/2007 ዓ/ም ከምሽቱ ሁለት ሰአት ተኩል ላይ። አቶ ሰይድ ይመር በተባለው ዜጋ መገደሉን የገለጸው መረጃው። ገዳዩም ያለአንዳች ችግር በአካባቢው ነዋሪ ተባባሪነት ማምለጥ እንደቻለ መረጃው አስታወቋል፣
    ህዝቡን ሲያንገላታ የነበረው የኤልሻል ቀበሌ አስተዳዳሪ የተገደለው። ማታ ላይ ወደ ሠርግ እየሄደ በነበረበት ሰአት መሆኑን። መረጃው አክሎ አስረድቷል፣