Sunday, April 12, 2015

በቤተመንግስት ጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩት የስርዓቱ ወታደሮች ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፤ ጉባ ወረዳ መቀየራቸው ተገለጸ፣



በመረጃው መሰረት። የአየር ሃይል አባላት ሆነው በቤተ መንግስት ዙርያ ጥበቃ ላይ ተሰማርተው የቆዩት ወታደሮች። መጋቢት 2/2007 ዓ/ም ይዘውት የነበረውን መሳሪያ አስቀምጠው ሌላ መሳሪያ በመታጠቅ። ግድቡ እየተሰራ ወዳለው ጉባ ወደ ተባለው ወረዳ እንዲሄዱ መደረጉን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣
    የኢህአዴግ ስርዓት። ከአባይ ግድብ ጋር በተያያዘ ስጋት ላይ ስለሚገኝ። ቀደም ሲል በርካታ የሰራዊቱ አባላትን ወደ አባይ ግድብ እንዲሄዱ ቢያደርግም። ወታደሮቹ ግን እግራቸው ወዳመራቸው እየተበተኑ ስላስቸገሩት። ታማኝ በሚባሉ የሰራዊት አባላት እየተካቸው እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስተድቷል፣