Saturday, November 21, 2015

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የሚገኙ የሰረአቱ ባለ ስልጣናት ለኢንቨስተሮች ተብሎ የሚሰጥ መሬት በማከፋፈል ሂደት አድሎዎ እየፈፀሙ እንደሚገኙ ተገለፀ።



        በመረጃው መሰረት በአማራ ክልል  ጎንደር ከተማ ለግል ባለ ሃብቶች ቤተ-እስራኤላውያን የሆኑት ኢንቨስተሮች የሚሰጥ  መሬት የስረአቱ ባለ ስልጣኖች በአፈፃፀሙ ሂደት በጉቦና በአድሎዎ እየፈፀሙት እንደሚገኙ ከገለፀ በኃላ። ጉቦ ላልሰጧቸው የግል ባለሃብቶች ግን ለድካምና ለእንግልት  እየተዳረጉ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ የስርአቱ ባለስልጣኖች በጎንደር ከተማ እየፈፀሙት ያለ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመሄድ ላይ ስላለ የከተማው ነዋሪ ህዝብ በበኩሉ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማመልከቻ እንዳቀረበ የገለፀው  መረጃ በተለይ ደግሞ የቅማንት ብሄረስብ በስረአቱ ተደጋጋሚ በደል እየደረሰበት ስለሚገኝ ተቃውሞ ሲያሰማ መቆየቱ ይታወሳል።