Wednesday, January 1, 2014

በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በታህሳስ 20/2006 አ/ም፣ “ዓረና ትግራይ” በተባለው ተቃዋሚ ድርጅት የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስርኣቱ ተላላኪዎች እንደተሰናከለ ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣




በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን፣ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ለሚገኝ ህዝብ አላማው ለማስተዋወቅና ፖለቲካዊ እቅስቃሴዎች ለማካሄድ በማሰብ በዓረና ድርጅት የታቀደው ህዝባዊ ስብስባ ለማሰናከል፣ የከተማው አስተዳዳሪዎች አስፈላጊ የሆነ ቅድመ ዝግጅነት ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ፣ ስብሰባ እንዲካሄድለት በታሰበው አዳራሽ ውስጥ ራሳቸውና ጭፍሮቻቸው በመገኘት፣ ስብሰባው እንዲቛረጥ ለማስቻል የተቻላቸውን ሁሉ እንዳደረጉ የደረሰን መረጃ ገለፀ፣

     በመረጃው መሰረት የዓረና ድርጅት በታህሳስ 20/2006 አ/ም የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በሽሬ ነዋሪ ህዝብ ትልቅ ተቐባይነት አግኝቶ ከጥዋቱ 2፣00 ሰአት ጀምሮ በርከት ያለ ህዝብ ወደ መሰበብያው አዳራሽ መሄድ በጀመረበት ግዜ፣ የከተማው ከንቲባ ተክላይ መረሳ፤ የደህንነት ሃላፊ የሆነው በየነ የተባለ ግለሰብና የፌደራል ፖሊስ አብረው ወደ ቦታው በመድረስ፣ በቦታው ለተገኘው ህዝብ መታወቅያ ወረቀት ሳትዩዙና ሳትፈተሹ ወደ አዳራሹ አትገቡም በማለት አስፈራርተው ለመመለስ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድተዋል፣

     ህዝቡን በማስፈራራት አላማቸው ያልተሳካው የስራአቱ ካድሬዎችና ኣጨብጫቢዎች፣ ያን ሁሉ ያዘጋጁት መሰናክል አልፎ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሹ ይጎርፍ የነበረው የከተማው ህዝብ እየጨመረ በመሄዱ፣ የስራአቱ ባለስልጣናት ሃሳባቸው ቀይረው የአባልነት ካርድ የያዘ ይሁን ያልያዘ እንደፈለገ ወደ ስብሰባው መግባት ይችላል ከማለታቸው በላይ፣ ለማስመሰል ሲሉ ህገ-መንግስቱ ላስቀመጠው የመሰብሰብና ሃሳብህን በነጻ የመግለፅ መብት ደጋፊዎች በመምሰልና ራሳቸውም ጭምር ወደ አዳራሹ በመግባት፣ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ዓረና አልቃይዳ ነው፤ ዓረና ፀረ ህዝብና አሸባሪ ነው በማለት መድረኩን እንዳወኩትና፣ የአረና አባል ለሆነው አቶ አስገደ ገብረስላሴ እየተናገረበት ለነበረው ማይክሮፎን በሃይል በመንጠቅ ስብሰባው እንዲቛረጥ ማድረጋቸው ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣