Wednesday, January 1, 2014

በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት በአገሪቱ ውስጥ ላሉ መማህራን ስለ ደሞዝ ጭማሪ የገባላቸው ቃል ባለመተግበሩ ምሬታቸውን አሰሙ፣




በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች  አብላጫ የስራ አፈፃጸም አሳይተዋል ተብለው በሞዴልነት ለሽልማት የታጩት፣ የገጠር መንገድ፤ ውሃ ሃብት፤ ጤና ጥበቃ፤ የትምህርትና የግምሩክ መስሪያ ቤቶች የእድገትና የሽግግር ትራንስፎርሜሽን ሂደት በተሳካ መንገድ እንዲቀጥል አስችለዋል በማለት፣ ለሰራተኞቻቸው የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግላቸው በስርአቱ በተገባላቸው ቃል መሰረት ለሌሎች ሲጨምር፣ በትምህርት መስሪያ ቤት ብቻ ተግባራዊ እንዳልሆነ ያገኘነው መረጃ አስታወቀ፣
    
      በስርአቱ የደመወዝ ጭማሪ ይደረግላቹሃል የሚል ቃል ከተገባልን   ስድስት ወር አልፎበታል ያሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተማሪዎች፣ ከላይ እንደተገለፀው ለተጠቀሱት መስሪያ ቤቶች የደመወዝ ጭማሪው ተግባራዊ ሲሆንላቸው፣ በመምህራን ብቻ ሳይተገበር መቅረቱ፣ ስርአቱ አንዱን ከሌላው እየለየ የሚያደርገው ህገ ወጥ አሰራር አሳዝኖናል በማለት፣ መምህራኑ ቅሬታቸው እንደገለፁ ለማወቅ ተችለዋል፣

     ይህ በእንዲህ እንዳለ ለመማህራኑ የሚከፈላቸው ውስን ደመወዝ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ባለው የገበያ ንረት የተመጣጠነ ክፍያ ባለመሆኑ ኑሮአቸው ለመምራት ተቸግረውና፣ በስርአቱ ቅጥ ያጣ አሰራር የተነሳም የሚወዱትን የአስተማሪነት ሞያ ትተው ለመውጣት እንደ አማራጭ ይዘውት እንዳሉ ከከተማው የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቀዋል፣