Sunday, October 12, 2014

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ከልክ ያለፈ ግብር እንዲከፍሉ እየተጠየቁ ባሉበት በአሁኑ ግዜ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ንግድ-ቤታቸውን በመዝጋት ላይ እንዳሉ ታወቀ፣





በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሸራሮ ከተማ በተለያዩ የንግድ መስክ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ግብር እንዲከፍሉ በገዢው ስርዓት ተልከው በመጡ ካድሬዎች እየተገደዱ መሆናቸውና ቀደም ሲልም ያፈሩት ሃብታቸውን ሽጠው እየከፈሉ እንደሚገኙና፤ በእንዲህ አይነት መንገድ ተሰርቶ የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ንግድ ፍቃዳቸውን ተረከቡን እያሉ እንዳሉ ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ታውቋል፣
    ከአቅማቸው በላይ ግብር እንዲከፍሉ ከተገደዱትና የንግድ ቤታቸው ከተዘጋባቸው ነጋዴዎች ለመጥቀስ ያህል።-
1. ጉዕሽ ፎቶ የሰላም ሆቴል ባለቤት የሆነው  2 ሚልዮን ብር
2. ሽሻይ ማርቆስ የሰሊጥ ነጋዴ
3. ገብረ ታረቀ የሸቀጣሸቀጥ ነጋዴ የሚገኙባቸው በርከት ያሉ ነጋዴዎች ሃላፊነት በማይሰማቸው መሪዎች የግብር አከፋፈል ምክንያት ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፣