በምንጮቻችን መረጃ መሰረት
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲ-ግራት ከተማ የሚኖር መላው ህብረተሰብ ለዕለታዊ ኑሮው የሚያስፈልጉት አላቂ ነገሮች በገበያ ላይ ሊያገኛቸው ባለመቻሉ ምክንያት ለችግር መጋለጡንና
በተለይ ደግሞ እንደ ዘይት፤ ስኳር፤ ፊኖ ዱቄትና ሌሎች ለኑሮው አስፈላጊ ነገሮች ከገበያ ጠቅልለው ከሚጠፉ ብዙ ጊዜ ስላስቆጠሩ፤ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ
እንዲያደርጉላቸው ምሬታቸውን እያሰሙ እንዳሉ ታወቀ፣
የአላቂ ነገሮች ከገበያ መጥፋት ምክንያት የሆነው በስርአቱ ለህዝቡ እንዲያከፋፍሉ
ተብለው የተቀመጡት ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ሲሆኑ። ለህዝብ ሊያከፈፍሉት የተረከቡትን እንደ ዘይትና ስኳር የመሳሰሉ አቅርቦት እየደበቁ
ለነሱ በሚጠቅም መንገድ ውስጥ ለውስጥ እየሸጡት እዳሉ ተገለጸ፣
በሌላ በኩል የከተማዋን ህዝብ በፒያሳ መሃል የሚገኝ ፋውንቴን መስሪያ
እንዲውል በማለት ያዋጡት 60ሺህ ብር በስራ ላይ ሳይውል ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው በህዝቡ የተገመገመው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ተስፋአለም ደስታ፤ ይህን ተከትሎ ወደ መቐለ ከተማ እንዲቀየር ስላደረጉት፤ ህዝቡ ደግሞ
ሙስና የፈጸመ ሰው በህግ እንዳይጠየቅ ብለው የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ቀይረውታል በማለት በስርአቱ ያላቸውን ተቃውሞ በመግለጽ ላይ እንደሚገኙ መረጃው አስረድቷል፣