Sunday, November 2, 2014

የኢህአዴግ ገዢ ስርአት ታማኝ ሁነው ሲያገለግሉ የቆዩትን የደህንነት አባላት ከተቃዋሚዎች ግንኝነት አላችሁ በሚል ምክንያት እየታሰሩ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስታወቀ፣




    በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በኢህአዴግ ባለ-ስልጣናት የደህንነት አባላት ተብለው በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተመድበው ሲሰሩ ከቆዩት ሳሚ የተባለ ግለሰብ፤ ጥቅምት 9/2007 ዓ/ም በበላይ አመራሮቹ ወደ መቐለ እንዲመጣና የግምገማ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፍ ከተደረገ በኋላ፤ ጌታቸው አሰፋ በተባለው   ባለ-ስልጣን በተመራ ስብሰባ ላይ ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኝነትና ትብብር እየፈፀምክ ቆይተሃል በሚል የሃሰት ውንጀላ፤ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ እንዲታሰር መደረጉ ተገልጿል፣ 
    ይህ በአፋርና በትግራይ ክልል ተሰማርተው እየሰሩ በቆዩት የደህንነት አባላት ላይ የተደረገው ስብሰባ፤ ባሁኑ ግዜ በስርአቱ እምነት ስላልተጣለባቸው  ምርጫው ከመድረሱ በፊት ከስራቸው ለማባረርና እስርቤት ውስጥ አስገብተው። በሌሎች ታማኞች ለመተካት የታሰበ ሴራ እንደሆነና፤  አሁንም ቀደም ብለው እስር ቤት ካስገቡት የደህንነት አባል ጋር ግንኝነት ነበራቸው ያሏቸውን ግለሰቦች ለማሰር ተንኮል እያበጁ መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣