የኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ሰራዊት
የሚመሩ ከፍተኛ ባለስልጣናት እርስ-በርሳቸው እንደማይስማሙ የገለፀው መረጃው፤ ከእነዚህም መካከል አንዱ ሻለቃ ወለምህረት የተባለ
የሰሜን ዕዝ የስለያ አባል ሆኖ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፤ በራህለ ከተማ ሂዶ ሰው እንዲያፍን ከሃላፊው የተሰጠውን መመሪያ ስላላመነበት
አላደርግም በማለት ትዕዛዙን እንደተቃወመው ታውቋል፣
በዚህ የተቆጡ ከፍተኛ አመራሮች ሻለቃ ወለምህረትን ወደ መቐለ በመውሰድ ለበርካታ
አመታት ሲሰራ ከቆየበት ስለያዊ ስራ የተባረረ ሲሆን፤ ይህን የማባረር ተግባር እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጠው ደግሞ ኮሎኔል አብራሃም
ማውጫ የተባለው የሰሜን ዕዝ የስልያ ሃላፊ እንደሆነ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣