በትግራይ ሰሜናዊ
ምዕራብ ዞን የመደባይ ዛና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋይ ብርሃነ የተባለ የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬ ለተለያዩ ህዝባዊ አገልግሎቶች
እንዲውል ተብሎ የተረከበውን ሁለት ሚሊዮን ብር በዚህ ሰሞን ይዞት እንደተሰወረ የገለፀው መረጃው በፈፀመው የሙስና ወንጀልም በሚመለከተው
የህግ አካል ቀርቦ እንዲጠየቅ የተደረገ ክትትል ባለመኖሩ የተነሳ ሊያዝ አለመቻሉን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
በተጨማሪ ደግሞ ምክትሉ ሆኖ ሲሰራ የነበረው አቶ ጎይቶም ገብረሃዋሪያ የተባለ
ካድሬ የካቲት 9/ 2007 ዓ/ም ከዘጠኝ መቶ ሺህ ብር በላይ የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ ይዞ ሊጠፋ ሲል ተይዞ በቁጥጥር ስር
የዋለ ቢሆንም በስልጣን ላይ የሚገኙት የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች
ግን ውስጣቸው ምን ያህል በስብሶ እንደሚገኝ የሚያመላክት ነው ሲሉ አንዳንድ ምሁራን በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን
አክለው ገልፀዋል።