Thursday, April 2, 2015

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ አካባቢ ውስጥ በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት ካቢኔ አባላቶች ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መጋቢት 18/2007 ዓ.ም የመግደል ሙከራ እንደተደረገባቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ዞን ልዩ ስሙ ይፍል በተባለ አካባቢ በብአዴን ኢህአዴግ ስርዓት የካቢኔ አባል በሆኑት ቁምላቸውና በተባለውና ዳኘ አይደፈር ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች መጋቢት 18 /2007 ዓ,ም ከምሽቱ 3።30 ሰዓት  ጥይት በመተኮስ የመግደል ሙከራ እንዳደርጉባቸው ለማወቅ ተችሏል፣
   መረጃው አክሎ ይህ በግፈኞች የኢህአዴግ ቡድን አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው የመግደል እርምጃ በጎንደር አካባቢ ብቻ እየተካሄደ ያለ ሳይሆን በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የህዝብ አመፅ ማሳያ መሆኑ። ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢ የደረሰን መረጃ አመልክቷል፣