በደረሰን መረጃ መሰረት በሁሉም የሃገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የመከላከያ
ሰራዊት አዛዦች በየደረጃቸው እረፍት በማይሰጥ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ። በተለይ ከኮሎኔል በላይ ያሉት የሰራዊት
አዛዦች ለ8 ቀናት የተሰበሰቡ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ ለ4 ቀኖች ውጥረትና የመረዳዳት መንፈስ ባልታየበት ስብሰባ ላይ እንደሰነበቱ
ከምንጮቻችን የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
በስብሰባው ላይ ከተነሱት መነጋገሪያ አጀንዳዎች መካከል የተወሰኑትን ለመግለፅ
ያህል ሰራዊቱ ለምንድን ነው ከያለበት የስራ ዘርፍ እየከዳ ያለው የሚልና። በማህበራዊ ጉዳይ ላይ ያለው ችግር፤ በአስተዳደር ያሉት
ችግሮች፤ እንዲሁም በጠላት ያለው ወቅታዊ ሁኔታና መሰል ተዛማጅ ነገሮች የሚመለከቱ በስብሰባው ላይ መነጋገሪያ አጀንዳ ሁነው የተነሱ
ሲሆን። እነዚህ የተነሱ ነጥቦች አብዛኛዎቹ በሚመለከታቸው አካላት ያልተመለሱ በመሆናቸው። ከኮለኔል በላይ ያሉት የስርዓቱ የሰራዊት
አመራሮች ለ3ኛ ጊዜ ተመልሰው ለመሰብሰብ እንደተገደዱ የደረሰን መረጃ አክሎ አስረድቷል፣