ከክፍለጦሩ ውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት።
በምዕራብ እዝ 24ኛ ክ/ጦር የገዢው ኢህአደግ ጉጅሌ የሰራዊት አባላት በሚቀጠሩበት ወቅት በስርአቱ የሚገባላቸው
ቃል ሰለማይተገበር ካላቸው የማህበራዊ ችግር የተነሳ መሳሪያዎቻቸውንና ትጥቃቸውን እየሸጡ በመጥፋት ላይ እንደሚገኙ ከገለፀ በኋላ።
በተለይ ደግሞ የክፍለ ጦሩ አባላት 2ኛ ረጅመንት የሆኑት ሁለት ወታደሮች መጋቢት 20/ 2007 ዓ/ም ክፍላቸውን
ትተው ዳንሻ አልፈው በጎንደር መንገድ በመሄድ ላይ እያሉ ለሲቪሉ ማህበረሰብ መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን ግዙን መሳፈሪያ አጥተናል እንዳሏቸው ሊታወቅ ተችሏል፣
መረጃው በማከል እንዳስረዳው። የክፍለ ጦሩ አዛዦች ለሰራዊቱ የማህበራዊ አገልግሎት ተብሎ የመጣውን ገንዘብ። ከታች እስከ ላይ ተሳስረው ለግል ጥቅማቸው
እያዋሉት መሆናቸውን በሰራዊቱ ተገምግሞ ሲያበቃ። እስከ አሁን ድረስ ግን የተተገበረ ለውጥ እንደሌለ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣