በምንጮቻችን
መረጃ መሰረት። በትግራይ ስሜናዊ ምእራብ ዞን በአዲ-ነብሪኢድና አካባቢዋ የሚገኙ የ31ኛ ክ/ጦር መካናይዝድ አባላት አቶ ሓጎስ
ለተባለ ንፁህ ወገን፤ ወጣቶች እየቀሰቀስክ ወደ ትህዴን ትልካለህ በሚል የሃሰት ውንጀላ። የ31ኛ ክ/ጦር የ4ኛ
ሬጅመንት ዋና አዛዥ የሆነው ኮለኔል አብርሃ። መጋቢት 25/ 2007ዓ/ም ከለሊቱ 6።30 ከቤቱ በማስወጣት እየደበደበ በመውሰድ
ሲመረምረው እንዳደረ የገለጸው መረጃው።። ጥዋት ወደ አዲነብሪኢድ ፖሊስ ጣቢያ አስተዳደር በመውሰድ በተከለከለ ሰአት ወደ ካምፓችን
ሲገባ ነው የያዝነው በሚል ሰንካላ ምክንያት አስሮ እንዳስረከበው የአይን እማኞች ገለፁ፣
ይህንን እኩይ ተግባር የሰሙት የአዲ-ነብሪኢድና አካባቢዋ ነዋሪዎች ደግሞ።
ሲቪል ሰው የሚያስጠይቀው ካለ በህጋዊ መንገድ መጣራት እያተገባው በወታደሮች መገረፍና መታሰር አይገባም፤ በቦታችንስ እስከ መቼ
ነው በሆነና ባልሆነው የምንሰቃየው በማለት በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ላይ ያላቸው ጥላቻ በከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ምሬታቸውን በመግለፅ
ላይ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣