Tuesday, April 7, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ አምሃ ደስታ በሚባለው ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን ለአባይ ግድብ እያወጣነው ያለው ገንዘብ በአመራሮች እየተበላ ነው ሲሉ ብሶታቸውን ገለፁ፣



  በደረሰን መረጃ መሰረት በእንጦጦ አምባ በተለምዶ አመሃ ደስታ በሚባለው 9ኛና 10ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን በተደጋጋሚ ለህዳሴ ግድብ እያወጣነው ያለው ገንዘብ በትምህርት ቤቱ  አመራሮች እየተበላብን ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር  መሃሪ ገብረሂወት ከወረዳው የድርጅት ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ጋር በመሆን ለግል ጥቅሙ ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል፣
   ያወጣነው ገንዘብ በአመራሮች ተበላብን ካሉት ወገኖች መካከል የተወሰኑትን ለመጠቀስ ያህል መምህር አቡነው የተባለው የታሪክ መምህር። ተክሉ ካሳ የተባለው የጂኦግራፊ መምህር። በላይ ሰብስቤ የፊዚክስ መምህር እንዲሁም መልሰው ታፈረ። ላዋየው ነጋና ዘመኑ የተባሉት መምህራን ብሶታቸውን መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል፣