Tuesday, April 7, 2015

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ምክንያት ለሞት እየተጋለጡ መሆናቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣



እንደ ምንጮቻችን ገለፃ በቅጥር ግቢው ውስጥ ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር የምግብ ጥራት ጉድለትና የካምፓሱ መልካም አስተዳደር ችግር መከሰቱን ተማሪዎች ተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ሲገልፁ የቆዩ ቢሆንም። እስካሁንም ግን ጉዳዩ ሊቀርፍ እንዳልቻለና። በውሃ ምክንያት የበርካታ ተማሪዎች ህይወት እየተቀጠፈ መሆኑንና በቅርቡ ብቻ እንኳን አንዲት  የደቡብ ክልል ተወላጅ ሴት  ተማሪን ጨምሮ 3 ተማሪዎች በውሃ ወለድ በሽታ ለሞት እንደተጋለጡ ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ተከልክሎ የነበረውን የምርጫ ካርድ እንዲሰጣቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በተከታታይ ለ15 ቀናት ታድሎ ሲጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ፕረዝደንት አቶ ጥላየ ጌቴ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.ን ምረጡ የሚል ቅስቀሳ ሲያስተጋባ እዚህ ውስጥ ቅስቀሳ ማድረግ የተከለከለ ነው በማለት የተቃወሙት ተማሪዎችም መድሃኒት የሌለው ባዶ ሆስፒታል የሚገነባ መንግስት አንመርጥም ማለታቸውን ታውቋል፣