Friday, May 15, 2015

በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ምድረ ፈላሲና አካባቢዋ ከሚገኙ የኢ.ህ..አ.ዴ.ግ ወታደሮች የምክትል አስር አለቃ ማእርግ ያለው ወታደር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።



በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ምድረ ፈላሲና አካባቢው ከሚገኙት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ስርዓት ወታደሮች መካከል አሊ አራጌ የተባለ ምክትል አስር አለቃ ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በፈቃድ ወደ አዲ ነብሪ ኢድ በሄደበት ጊዜ ማንነቱ ባልታወቀ ገዳይ ሚያዝያ 23 ቀን 2007 ዓ/ም በአከባቢው በሚገኘው ካምፕ ሞቶ እንደተገኘ ታውቋል።
    ይህ የተገደለው ወታደር በማን እንደተገደለ በሃላፊዎች ምንም ዓይነት የተደረገ ምርምራ ሳይኖር መቀበሩን የገለፀው መረጃው የአካባቢውን ህብረተሰብ ከሰራዊቱ ለመነጠል የዚህ አካባቢ ህዝብ የትህዴን አባል ነው የሚል ወሬ  ከሰራዊቱ አዛዦች መናፈሱን የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።