በመረጃው መሰረት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን
የሚገኙ የስርዓቱ አስተዳዳሪዎች በመጪው የይስሙላ ምርጫ ለመቀስቀስ ተብሎ በገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ስርዓት የተለጠፈውን የንብ
ምልክት ፖስተር ቀድዳችኋል በሚል ሰንካላ ምክንያት ዜጎች በዞኑ አስተዳዳሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲጠመዱና እንዲታሰሩ እየተደረገ እንደሆነ
ተገልጿል።
የታሰሩ ዜጎች
ፖስተር መቅደዳችንን የሚመሰክር ማስረጃ አቅርቡልን ወይም እንፈታ ስልጣናችሁን ተጠቅማችሁ ባልዋልንበት ወንጀል ልታስሩን አይገባም
ሲሉ አቤቱታ ማቅረባቸውን የገለፀው መረጃው አቤቱታ ካቀረቡት እስረኞች መካከልም አቶ ገመቹ፤ አቶ ያሲን አበራና ሌሎችም እንደሆኑ
ለማወቅ ተችሏል።