Sunday, September 6, 2015

በሽሬ እንዳስላሴ መብራት ጠቅልሎ በመጥፋቱ የድርጅት ባለቤቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን ነሃሴ 13/2007ዓ/ም በተከሄደው ስብሰባ ላይ ተገለፀ።



     በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የሚኖር ህዝብ በከተማዋ መብራት ጠቅልሎ ከጠፋ ረጅም ጊዜ ቢያስቆጥርም መፍትሄ ሊደረግለት ባለመቻሉ ምክንያት ባለሆቴሎችና ባለምግብ ቤቶች ስራቸውን በማቆም ለኪሳራ መጋለጣቸው የስርአቱ ባለስልጣናት ቢያውቁም እንኳን ዘላቂ መፍትሄ ሊያደርጉላቸው ይቅርና ግዚያዊ መፍትሄ ሊሰጡ ባለመቻላቸው ባለሃብቶቹ ምሬታቸውን በመግለፅ ላይ እንዳሉ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገልጸዋል።
      ከነዚህ በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ለኪሳራ ከተጋለጡት ባለ ሃብቶች መካከል የካሌብ ሆቴል ባለቤት፤ የዳሽን ሆቴል ባለቤት፤ የቃሌማ ምግብ ቤት ባለ ቤትና ሌሎች የሚገኙባቸው ሆነው ባለሃብቶቹ በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ካለፉት ስርአቶች የማይለይ ስርአት ነው በማለት እንደተናገሩ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፖሊሶች የሚለብሱትን የደንብ ልብስ ለብሰው እንደሽፋን በመጠቀም  ከሌቦች ጋር በመመሳጠር መብራት ሲጠፋ እየሰረቁን ነው፤ ፖሊሶች ከሌቦች ጋር በመተባበር ስለሚሰሩ ሲሰርቁ አይተን ያመጣናቸው ሌቦች በመልቀቅ ለተበዳዮች ያስሯቸው በማለት ህዝቡ መሬቱን በማሰማት ላይ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።