Sunday, September 6, 2015

በታህታይ አድያቦ ወረዳ በከብት አርቢነት ስራ የሚነሳቀሱ ዜጎችን አግባብነት በሌለው መንገድ ገንዘብ ክፈሉ እየተባሉ እየተገደዱ እንደሚገኙ ተገለፀ።



     ምንጮቻችን በላክሉን መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ ሸራሮና ማይ-ሓንሰ አካባቢ የሚኖሩ ስርአቱ ያሰማራቸው የኢህአዴግ ካድሬዎች በሰንበል አካባቢ እየተንቀሳቀሱ ለሚገኙ አርሶ-አደር ከብት አርቢዎች በመያዝ ለአንድ ከብት 150 ብር ቅጣት እያስከፈሏቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
     ይህ በእንዲህ እንዳለም አንከፍልም ለሚሉት ከብት አርቢዎች ደግሞ በግድ ይዘው ህዝባዊነትና ሃላፊነት ወደ ማይሰማው የስርአቱ ፍርድ ቤት በመውሰድ ለ3 ወር እንዲታሰሩ በማስፈረዳቸው የተነሳ በወረዳው ውስጥ ግጭት ተከስቶ እንዳለ መረጃው አክሎ አስረድቷል።