በአዲግራት ከተማ ያለው ስር የሰደደ የመብራት
አቅርቦት ችግር ለመፍታት ለዝርጋታና ለእድሳት በሚል የተመደበ 4
ሚሊዮን ብር በስራ ላይ ሳይውል በባለስልጣናት ስለተጠፋፋ መብራት ማግኘት የሚገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች በጨለማ ተውጠው እንደሚገኙ
ታወቋል።
መብራት ካላገኙ አካባቢዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጠቅስ ያህል ከፒያሳ
እስከ ሃዲሽ አዲ መብራት የሌለው ከየዶክተር መንገሻ አከባቢ እስከ ካምቦ፤ ከፒያሳ እስከ ሆስፒታል፤ ከመቐለ መንገድ እስከ ዛላምበሳ
መስመር ያለውና ሜዳ አጋመ አካባቢ የሚገኙ ቦታዎች ጠቅልለው መብራት አግኝተው እንደማያውቁ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
