በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በውጭ ሃገር የሚገኙ
የተምቤን ተወላጆች እንዲሁም የተንቤን ነዋሪዎች በአሉላ አባ ነጋ ስም የዩንቨርስቲ ቅድመ ዝግጂት ትምህርት ቤት ፕሪፓራቶሪ ለመስራት
ብለው ያዋጡት በርካታ ገንዘብ የኢህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ግን የታሰበውን ግንባታ አቋርጠው ለመለስ ፋውንዴሽን እንዳዋሉት ሊታወቅ
ተችሏል።
ከዚህ በመነሳትም ህዝባችን እኛ ለመለስ ፋንዴሽን
መሲያ ሳይሆን ያወጣነው ለሃገራችንና ለአፍሪካ ኩራት ለሆነው አሉላ አባነጋ መታሰቢያ እንዲሆን ለትምህርት ቤት መስሪያ ነው በማለት የተቃውሞ ጥያቄ አንስተው የሚመልስ አካል ስላልተገኘ በህዝቡና
በካድሬዎች መካከል ከባድ ውጥረት ነግሶ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
