በመረጃው መሰረት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምርጫ
1997 ዓ/ም ከቅንጅት መሪዎች ጋር አብሮ ታስሮ የተለቀቀ ሲሆን፣
ቀደም ብሎም ከፅሁፍ ስራው ጋር በተያያዘ ከ5 ጊዜ በላይ ታስሮ እንደነበረና ያለፉትን ሶስት አመታትም በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ቤት እንዳሳለፈና አሁንም ለ18 አመታት እስራት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ
ነው።
የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስራዎቹ ድንበር ተሻጋሪዎችና
አስተማሪዎች መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የፅናት ምልክት ተደርጎ ስለ ሚቆጠር
የ5 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ሽልማት በ36ኛው የአለም አቀፍ ፃሃፊዎች ቀን ላይ እንዲበረከትለት በፕሮግራም እንደተያዘ
ተገለፀ።
በተመሳስይ የጋዜጠኛ እስክንድርን መታሰር አግባብነት የሌለውና አለም አቀፍ ህግን የጣሰ መሆኑን በመጥቀስ እንዲፈታ የተባበሩት መንግስታት
ድርጅት የሰብአዊ መብት ቡድን በተደጋጋሚ መጠየቁን መግለጫው አስታውቋል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ጋዜጠኛ እስክንድር ከሶስት አመታት በፊት
የፔን ባርባራ ጎልድ ስሚዝ ፍሪደም ቲ ራይት ባለፈው አመት አምና
ደግሞ ጎልደን ፔን አዋርድ ኦፍ ፍሪደም አሸንፎ መሸለሙ ታወቀ።
በመጨረሻ መረጃው ገዥው የኢህኣዴግ ስርኣት ጋዜጠኛ እስክንድር
ነጋ ጋዜጣ የማተም ፈቃድ የተከለከለበት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የስርዓት መውደቅና ለውጥ አይቀሬ መሆኑን ማስረጃዎችን የያዙ ፅሁፎችን
በማህበራዊ ድረ ገፆች በማጋለጥና ለስርአቱ ስጋት ስለ ሆነበት መሆኑ ተገለፀ።