Friday, November 6, 2015

በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል የሚገኙ የሃመር ህዝቦቸ አጋጥሞት ባለው ድርቅ ምክንያት 25% የሚሆነው ህዝብ እርዳታ ጠባቂ ከመሆኑ ምክንያት ተሎ የሚደርስላቸዉ መንግስት ኣካል ባለመኖሩ በምግብ እጥረት እየተጎዱ መሆናቸው ተገለፀ።



   በደረሰን መረጃ መሰረት በደቡብ ክልል ሃመር አካባቢ  በህዝቡ ላይ አጋጥሞት ያለው ድርቅ በሰውና በእንስሳት ከፈተኛ የምግብ ችግርና ከባድ አደጋ ላይ በመወደቁ ምክንያት በተለይ በአሁኑ ውቅት  በጠቅላላው የዚህ ኗሪ ህዝብ 25% የሚሆነው። የእርዳታ ጠባቂ ሆኖ በሚገኘበት ሰአት ገዢው መንግሰት እርዳታ ሊያገኝ ባለመቻሉም የተነሳ ህዝቡ ድርቅ በፈጠረው ችግርና ስቃይ ውስጥ ገብቶ እንዳለ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
   መረጃው በማስከተል በስልጣን ላይ ያለው ስረአት በኢትዮጵያ  ያለው ፈጣን እደገት ለሶስት አመት ለድገተኛ አደጋ ሊውል የሚችል ሃብት ሰብስበናል እያሉ ሲናገሩ ቢቆዩም  አሁን ግን በአገር ደረጃ በድርቅ ተይዞ ያለው 8.5 ሚሊዮን ህዝብ  ለመመገብ 500 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ሲታወቅ። ለአለም የእርዳታ ለጋሽ  አገሮች ልመና መጠየቅ መልእክት እያስተላለፈ ይገኛል፣ ከዚህ በፊት   ለሶሰት አመት  ለድንገተኛ አደጋ የሚሆን ገንዘብና ሃብት አለን የሚባለው አነጋገር የነበረው ይቅርና ለሶሰት ወር የሚሆን መመገብ አቅቷቸው እጃቸውን ወደ ልመና መዘርጋትና መቅረብ  እስከ አሁን ድረስ ሲናገረው የነበር ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ መሆኑን  የአገሩና የአለም ህዝብ ለማደናገር የተጠቀመው ስልት እንደሆነ  የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረደቷል።