Friday, November 6, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘው የኢትዮጵያ መሬት በእርሻ ስራ የተሰማሩት ኢንቨስተሮች ውስጥ የሚገኝ ካምፕ በሱዳን ወታደሮች ተቃጥሎ ሰራተኞች ደግሞ እንደተገደሉ ታወቀ።



    ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት፦ በሰሜን ጎንደር ዞን፤ ታች አርማ ጭሆና መተማ ወረዳዎች፤ በሚገኘው የኢትዮጵያ የእርሻ መሬት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኢንቨስተሮች በሱዳን ወታደሮች በሌሊት ካምቢያቸውን በእሳት ጋይቶ እዛው የሚሰሩ የነበሩ የቀን ሰራተኞች ደግሞ እንደ ተገደሉ ለማወቅ ተችለዋል።
    መረጃው አክሎ። በተለይ አቶ ኪዳነ የተባለ የአዲስ ኣበባ ነዋሪ የሆነ ባለ ሃብት በታሕታይ አርማጭሆ /የሱዳን ድንበር/ የታደላቸው ሰፊ የእርሻ መሬት፤ የሰሩት ካምፕ ከነሙሉ የማሽነሪው ንብረት በሌሊት ካቃጠሉት በኃላ ከፊታቸው ያገኙዋቸው ሰራተኞች ደግሞ እየገደሉ በመሄድ ላይ  በነበሩበት ጊዜ በገዢው ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ ሰራዊት ግን የተወሰደ እርምጃ እንደሌለ ተገልፀዋል።
    በኢህአዴግ ስርአት ዝምታ የተቆጣ የታሕታይ አርማጭሆ ወረዳ ነዋሪ ህዝብ ደግሞ ወንድሞቻችንና ልጆቻችን የሆኑ ዜጎች ያለ ምንም በደል በባእድ የሱዳን ወታደሮች ተገድለው መንግስት ለምን ግብር መልስ  አልሰጠም  በማለት አንድ ኣካል ሁኖ ተቃውሞና ግርግር በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህ የህዝብ ተቃውሞ የተደናገጡት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደግሞ ወደ አካባቢው የመከላክያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ አባላት እያስጠጉ እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።