በደረሰን መረጃ መሰረት ጥቅምት 8 /2008 ዓ/ም በአባይ ወልዱ
የሚመራ አስተዳዳሪ ቡድን ከአድዋ ከተማ ኗሪ ህዝብ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ከፋተኛ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸውና ለተቃውሞው መነሻ
የሆነው ደግሞ ከምርጫ በፊት ለህዝብ ቃል የተገባውን አልተተገበርም የሚል ሲሆን። ቃል ተገብተ ካልተሰሩት ስራዎች መካከል ውስጥ
ለመጥቀስ ያህል፦
1 ከራማ አዲአቡን ያለው መንገድ ስራ እናስተካክላለን
ያላችሁትን አልተስተካከለም
2 በአዲ አቡን በከተማ ውስጥ ሆስፒታል ለመስራት ተብሎ
መሰረት ድንጋይ የተቀመጠው ሳይሰራ ቀርቷል።
3 በአድዋ ከተማ ዩኒቨርሲቲ ይሰራል ተብሎ የነበረና ሌላም
በአባይ ወልዱ ለህዝብ ቃል የተግባለት ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ
አንድም ነገር ሊሰራ አልቻለም ህዝብ ደግሞ ለምን
እንሰራለን የተባለው ሳይሰራ ቀረ በማለት በውስጢ እንቅልፍ
የሚነሱበት ችግሮች ሊፈቱለት ባለመቻሉ ምክንያት ሃሳቡን በቁጣ እንዳቀረበ
ተገለፀ፣
የህዝቡን ጥያቄና ምሬት አስመልቶ አባይ ወልዱ የሰጠው መልስ እነ'ዛ
ኮንትራክተሮች መንግስት በቂ የሆነ ካሳ ሰለ ማይሰጥ ከቦታችሁ እንዳትፈናቀሉ በማለት ህዝቡ ስለ ቀሰቀሱ ነው ሲል የማድናገሪያ ሃሳብ ቢያቀርብም ህዝብ ግን የነበርው ስሚቱ የበለጠ እንደተባባሰበትና ለተሰጠው መልስ
እንዳልተቀበለው ከከተማው ያገኘነው መረጃ ጨምሮ አስርድቷል።