Wednesday, November 11, 2015

የሃገራችን ወጣቶች ፀረ-ህዝብ በሆነወን የኢህአዴግ ገዢ ሰረአት በመቃውም በየጊዜው ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራያሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በመግባት ላይ ይገኛሉ።



ለገዢው የኢህአዴግ ስርአት በመቃወም ወደ ትህዴ ከተቀላቀሉ ወጣቶች ስማቸውን ለመጥቀስ ያህል፦
1 ምዕባለ ተካ ከመእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ሰማሃል ቀበሌ
2  ሙሉ ሃፍቱ ከመእከላዊ ዞን መረብ ለኽ ምሕቛን ቀበሌ
3  የዕብዮ ገብረመስቀል ከስ/ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ  ወረዳ ዓዲ-ዳዕሮ ቀበሌ
4  ፋትዊ አውዓላ ከምስራቅ ዞን ኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ቀበሌ
5 ክብሮም ጣዓመ ከመእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ሰማሃል ቀበሌ
6 ሃፋቶም መንግስቱ ከምስራቅ ዞን ሳዕሰዕ-ፃዕዳ እምባ ወረዳ ፀንቃ-ኔት ቀበሌ
7  ሕሉፋ ብረሃነ ከምስራቃዊ ዞን ጉሌ-መኽዳ ፍረ-ዳሸም ቀበሌ የተባሉት የሚገኑባቸው ወጣቶች በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ማሰልጠኛ ማእከሉ የገቡ መሆናቸውን ተገለፀ፣
   ወደ ትግሉ ከተሰለፉት ወጣቶች መካከል የዕብዮ ገብረ መስቀል  እንደ ሰጠው መረጃ። በላዕላይ አድያቦ አካባቢ የሚኖር ህዝብ  በአብዛኛው በእርሻ ስራ ላይ በሚቀሳቀስበት ጊዜ በወያኔ ስረአት አመራሮች ከትህዴን ድርጅት ጋር እየተገናኛችሁ፤ የትህዴን ሬዴዮ ትሰማላችሁ እየተባሉ በጥርጣሪ አይን በማየት ክትትልና ቁጥጥር ስለ ሚያደርጉላቸው በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች የታሰሩ እንዳሉ ገልፆዋል።
     በማስከተል ወጣቱ  ለራሱ ከዓዲ -ዳዕሮ ወደ ዊዳኽ እንስሳት ለመጠበቅ በሚሄድበት ጊዜ ትህድን ጋር ለትገናኛለህ በሚል ተከሶ ለ5 አመት ያለምንም ወንጀል ተፈርዶበት ታስሮ ከቆየ በኃላ። ፍርዱን ጨርሶ እንደወጣና የገዢው ስርአት የተዛባ የፍርድ ውሳኔ ደግሞ በምሬት መውቀሱን ገለፀ።