Sunday, September 28, 2014

በአማራ ክልል ታች አርማጭሆ ወረዳ፤ አብራሃ ጅራ በተማለው ቦታ የሚኖረው ህዝብ አመጽና ግርግር ማስነሳቱን ምንጮች ከቦታው ገለፁ።



ምንጮቻችን በሰጡት መረጃ መሰረት በታች አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ አብርሃ ጅራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚኖር ህዝብ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት መስከረም 4/2007 ዓ/ም አመፅ እንዳስነሳና ለተነሳው ግርግር ለመከታተልም የአማራ ክልል የደህንነት ምክትል  አዛዥ የሆነው እቶ ወልደምህረት አባይ የተባለው የብአዴን ኢህአዴግ ልኡክ ወደ ቦታው ይጓዝ በነበረበት ግዜ በደንሻና በአብደራፍዕ አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ ራሱና ከሱ ጋር የነበረው ሌላኛው ሰው እንደሞተ ተገለጸ።
     እየተነሳ ያለው ህዝባዊ አመፅና ግርግር በታች አርማጭሆ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ያገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ያለ ችግር መሆኑን የገለጸው መረጃው እየተፈጠረ ላለው ግርግር መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ ምክንያት በህዝቡ መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት እየተባባሰ መቀጠሉን መረጃው አክሎ አስረድቷል።