Sunday, September 28, 2014

በእንዳባጉና ከተማና አካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች ወደ ውትድርና፤ ፌደራል ፖሊስና መደበኛ ፖሊስ እንዲገቡ በገዥው መደብ እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮች ከቦታው አስታወቁ።



    በተገኘው መረጃ መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ በእንዳባጉና ከተማና አካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች መስከረም 6/ 2007 ዓ/ም ወደ መከላከያ ሰራዊት፤ ፌደራል ፖሊስና መደበኛ ፖሊስ ሰራዊት እንዲገቡ ለማድረግ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ቢያስገድዷቸውም ተማሪዎቹና ቤተሰቢቻቸው ግን ልጆቻችን የሚማሩት ወታደሮችና ፖሊሶች እንዲሆኑ እይደለም በማለት ተቃውሞአቸውን እየገለፁ መሆናቸው ተገለጸ።
    መረጃው ጨምሮ አስተዳዳሪዎቹ ወደ ውትህድርና አንገባም ያሉትን ተማሪዎች ለማታለል ሲሉ መንግስት ወደ መከለከያና ፖሊስ ሰራዊት ከገባችሁ በኃላ የላቀ ሞያና ሃላፊነት እንድትይዙ ያደርጋችኋል በማለት ቢቀሰቅሳቸውም ተማሪዎቹ ግን እንዳልተቀበሉት መረጃው አክሎ አስረድቷል።