በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን በፀገዴና በወልቃይት ወረዳዎች የሚገኙ የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች
ለሚሊሻዎች ባካሄዱት ስብሰባ በሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት
ተፈራ የተባለ ሚሊሻ ተዘራ አድማሱ የተባለውን ሚሊሻ ተኩሶ እንደገደለው ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማከል የተዘራ አድማሱ ጓደኛ ለገዳዩ ተፈራ አስመላሽ እንደገደለው ከገለፀ በኋላ እንደዚህ አይነት የበቀል
እርምጃ በስርዓቱ ሚሊሻዎች መካከል የተለመደ ባህሪ መሆኑን በመግለፅ
ይህ ደግሞ ስርዓቱ በሚሊሻዎች መካከል አንድነት እንዳይኖራቸውና እንዳይተማመኑ የፈጠረው ብልሹ አሰራር እንደሆነ ታውቋል።
በተመሳሳይ ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ
ወረዳ ምድረ ፈላሲ ቀበሌ በሚገኙ ሚሊሻዎች መካከል ከባድ ውጥረት ሰፍኖ እንደነበር መግለፃችን ይታወሳል።