Saturday, January 24, 2015

በዓዲግራት ከተማ የሚገኙ የህወሓት ኢህአደግ ካድሬዎች ለመንግስት ሰራተኞች የምርጫ ካርድ ውሰዱ እያሉ እያስገደዱዋቸው መሆናቸውን ከከተማዋ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



     በከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት ጥር 1/ 2007ዓ/ም በዓዲግራት ከተማ የሚገኙ ለሆዳቸው ያደሩ የስርአቱ ካድሬዎች ለመንግስት ሰራተኞች የምርጫ ካርድ አውጡ፤ ፅህፈት ቤታችሁን ዘግታችሁ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ውጡ ብለው በሃይል እንዳስገደዷቸው ተገለጸ።
     በተመሳሳይ ከኢህአደግ ምርጫ ተስፋ ያጣ ህዝብ የምርጫ ካርድ እንዲውስድ እስከ ቤቱ ድረስ በመሄድ እያስገደዱት መሆናቸውና ካልወሰደ ግን ህጋዊ መብቱን እንደሚገፉት በማሳወቅ እያስፈራሩት እንዳሉ ታውቋል።
   ከምርጫ ጋር ተያይዞ  በህዝብ ሊነሳ በሚችለው ተቃውሞ የሰጉት የስርዓቱ ካድሬዎች ሴቶች ጭምር ሳይቀሩ በሌሊት ዋርድያ እየዞሩ እንዲጠብቁ እያስገደዱዋቸው መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።