Saturday, January 24, 2015

የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበራ ሃይለማሪያም 13 ሚሊዮን ብር የህዝብና የሃገር ንብረት ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው ተገለፀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በማከላዊ ትግራይ ዞን የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበራ  ሃይለማሪያም ከዚህ በፊት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሃገርና የህዝብ ንብረት በልተሃል ተብሎ ታስሮ ከቆየ በኋላ ታህሳስ 28 /2007 ዓ/ም ወደ ፍርድ ቤት በቀረበበት ጊዜ ደግሞ 13 ሚሊዮን ብር አጠፋፍተሃል ተብሎ በህዝብ  ክስ እንደተመሰረተበት ታውቋል።
በተጨማሪም ከንቲባው በተገለፀው ዕለት በ10 ሺህ ብር ዋስ ብቻ እንዲለቀቅ ከተደረገ በኋላ የአክሱም ከተማ ህዝብ ደግሞ ይህን ገንዘብ ለብቻው አይደለም የበላው የአባይ ወልዱ እጅም ስላለበት እንዳይጠየቅ ፈርቶ የእስረኛው ደጋፊ በመሆን መታሰር የለበትም እያለ ሲከራከር ቆይቷል፣ስለዚህ ይህ በሙስና ጉዳይ የተከሰሰው ግለሰብ ሳይመረመር በዋስ መውጣት የለበትም ከአባይ ወልዱ ጋር የተሳሰረ ስለሆነ ሁለቱም በአንድ ላይ መጠየቅ አለባቸው በማለት ህዝቡ ጥሪውን እያስማ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በስልጣን ላይ ያለው አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በአለም ማህበረሰብ ፊት ሙስናን የሚዋጋ በመምሰል ያሰጉኛል ያላቸውን አንዳንድ ሃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረዋል እያለ በእስር ቤት በማጎር የዋስ መብታቸውን እየከለከለ ለአክሱም ከተማ ከንቲባ ግን ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ላጠፋፋው በ10ሺህ ብር ዋስ ብቻ እንዲለቀቅ ማድረጉ በሃገራችን ምን ያህል የህግ የበላይነት እንደሌለ የሚያረጋግጥ ነው በማለት ነዋሪው ህዝብ እየተነጋገረበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።