በምንጮቻችን መረጃ መስረት በታች አርማጭሆ
ወረዳ ልዩ ቦታ አብርሃ-ጅራ በተባለ ከተማ በስራ ምክንያት የሚንቀሳቀሱ የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ የመኪና ሺፌሮች እየተገደሉ
መሆናቸው የገለጸው መረጃው ከተገደሉት ውስጥም ኤፍሬም ለገሰ የተባለው ሹፌር ከማይካድራ ወደ አብርሃ ጀራ ለስራ በሄደበት ሰዓት
ታህሳስ 29/2007 ዓ.ም እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው አክሎ ከአሁን በፊት በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል መካከል ተፈጥሮ
የነበረውን ግጭት ምክንያት በማድረግና ሁኔታውን ለማባባስ ሲባል የፖሊስ አባላት ሆን ብለው የፈፀሙት ጉዳይ ነው በማለት የአካባቢው ህብረተሰብ በሰፊው እየተነጋገረበት መሆኑን መረጃው አክሎ አስረድቷል።