Monday, January 26, 2015

ጥር 2 / 2007 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ለምርጫ ካርድ ጊዝያዊ መመዝገብያ ተብሎ የተተከለው ቴንዳ በሌሊት ተቃጥሎ ማደሩ ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ።



   በምጮቻችን መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ፤  ቀበሌ 16 ውስጥ በኢህአዴግ ቡዱን ለምርጫ ካርድ ግዚያዊ መመዝገብያ ተብሎ የተተከሉ 16 ቴንዳዎች ባልታወቀ ምክንያት ሌሊት ላይ በእሳት መቃጠላቸው ተገለፀ።
   በመመዝገብያ ጣብያ ያጋጠመውን የእሳት አደጋ የስርዓቱ የፀጥታ አካላት በማጣራት ስራ ላይ ቢሰማሩም በማን እንደተፈፀመ የታወቀ ነገር እንደሌለ የገለፀው መረጃው ህዝቡ ወደ ፊት የሚካሄደውን አስመሳይ ምርጫ ካርድ አንወስድም በማለት እንደተቃወመና እርምጃውም በዚሁ ምክንያት የተካሄደ እንደሆነ በርካታ ወገኖች እየተነጋገሩበት መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስረዷል።