Monday, January 26, 2015

የነቀምት ከተማ ነዋሪዎች የኢህአደግን ስርአት ብልሹ አሰራር በመቃወም ጥር 6/2007 ዓ/ም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።



   በኦሮሚያ ክልል የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የገዢውን ስርአት ብልሹ አሰራር በመቃወም ጥር 6/ 2007 ዓ/ም የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውና በዚሁ ተቃውሞ የሰጉ የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ፌደራል ፖሊሶችና መደበኛ ፖሊስ በማሰማራት ህዝቡን ደብድበው እንደበተኑት ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው ጨምሮ እነዚህ ነዋሪዎች በፍትህ እጦት እየወረደባቸው የቆየውን ችግር መፈትሄ እንዲደረግለት በማለት ከወር በፊት ጀምረው በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ቢቆዩም አስተዳዳሪዎቹ  የህዝቡን አቤቱታ ሰምተው መፍትሄ ማስቀመጥ ስላልቻሉ የመጣ ይምጣ በማለት ህዝብረተሰቡ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳካሄደና በዶክተር መራራ የሚመራው ፓርቲም በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተቀላቅሎ እንደነበር ታውቋል።