ሰላምን ከሚጠየፍ ስርአት ጉያ ሆነህ ሰለማዊ
ፖለቲካዊ ትግል ለመካሄድ ማሰብ ዜጎች ለሰላም የሚያድርጉትን ትግል ከማዳከም ውጭ ሌላ ውጤት መጠበቅ የዋህነት ነው።
የኢህአዴግ ስርአት ሰላምን የሚጠየፍ ስለ መሆኑ ጋሃድ ከሚያደርጉ ትላልቅ
ምሳሌዎች በትግራይና በኣማራ፤ በአፋርና ሶማል፤ በትግራይና አፋር መሃከል እስከ ደም ማፋሰስ እያደረሰ ያለ ግርግር ገዢው ስርአት
ሆን ብሎ ውስጥ ለውስጥ የሚማግደው እሳት ነው፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝቦች ኣንድነት መጠናከር ማለት የኢህወዴግ የስልጣን ዕድሜ
ማሳጠር ማለት ስለሆነ ልዩነታችን ከማንም ባእድ በላይ ስርአቱ የፈልገዋል።
በሃገራችን ውስጥ ያሉ ሰለማዊ ፖለቲካዊ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶች መደራጀታቸው
መልካም ሁኖ ምን ያህል ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ ግን የሁሉም ለውጥ ፈላጊ ህዝብ ጥያቄ ነው፣ እስከ አሁን እንደምናየው ከሆነ ለህዝብና
ለሃገር ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ስርአቱ ለፖለቲካ ፍጆታውና ለፖለቲካዊ
ትግል ዕድል የሚሰጥ ዴሞክራስያዊ ስርአት ሰፍነዋል ለማለትና ያለ ህፍረት ከምእራባዊያን አገሮች እጁን ዘርግቶ እርዳታ ለመቀበል
እየተጠቀመባቸው ነው።
በአንድ ላይ ተጠርንፈው ፈጣን እድገት ማምጣት እየተገባቸው በ90 ጉጅሌዎች
ተበታትነው ኣብዛኛዎቹ የገዢው ስርአት ዕድሜ ማራዘምያ ሁኖው እየቀጠሉ
ነው፣ እነዚህ ድርጅቶች ድርጅታዊ ነፃነት የሚባል የሌላቸው የገዢው ስርአት ካድሬዎች እንደፈለጉ እየገቡ የሚንደላቀቁባቸው ናቸው፣
በሌላ በኩል ደግሞ በድርጅቶቹ ውስጥ ተቃዋሚ ኣስመስሎ የራሱን ሰዎች በመላክ በመበታተኑ ስራ ላይ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው፣ ለሀቀኛ
ታጋዮቹ ሳይቀር በየግላቸው ግንኙነት በመፍጠር እየበደሉህ ነው፤ መሪ መሆን የነበረብህ አንተ ነበርክ፤ ከነሱ ካፈነገጥክ እናግዘሃለን
ወዘተ በሚሉ አጉል ተስፋዎች በመደለል እየበታተናቸው ይገኛል።
ይህ የኢህአዴግ
ቀኝ እጅና በኢህአዴግ ባለስልጣናት አድርግ አታድርግ እየተባለ የሚሰራ የምርጫ ቦርድ የዚህ እኩይ ተግባር ምሳሌ ነው፣ በፊዴራልና
በክልል የምርጫ ክልሎች ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኝነት እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነጻ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ
ይቋቋማል፣ የሚል በህገመንግስቱ
አንቀፅ 102 በቁ.1 ላይ ሰፍሮ ይገኛል፣ ይሁን እንጂ በሃገራችን ውስጥ ያለ የምርጫ ቦርድ ግን ኣሰራሩ ከመጠን በላይ ወደ
ገዢው መንግስት ያደላ ነው፣ ሰሞኑን ከሀላፊነቱ ውጭ በመስራት በድርጅቶቹ ውስጥ አላስፈላጊ ጣልቃ እየገባ እርስበርሳቸው አጣልቶ
ከምርጫ ለማግለል ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ሰንብተዋል፣ የምርጫ ወቅት በተቀራረበበት ግዜ ምክንያት መፍጠር፤ ያለ ምንም ዝግጅት
ጉባኤ እንዲካሂዱ ማስገደድ፤ ለውስጥ አሰራራቸው መቃወምና ስምምነት የላቸውም እያለ ጥላሸት እየቀባ ኢህአዴጋዊ ግዳጁን እየተዋጣ
ይገኛል፣ ተቃዋሚ ድርጅቶች የውስጥ ችግራቸውን ራሳቸው መፍታት እየተገባቸው ካልቻሉም በፍርድ ቤት መጨረስ እየቻሉ ምርጫ ቦርድ
አስታራቂ መስሎ በመሃላቸው በመግባት እየበታተናቸው መሆኑን እየታዘብን ነው።
በስርአቱ መጥፎ አስተዳደር
ትእግስቱ የጨረሰ ህዝብ ግን በምርጫ ያለው ተስፋ ሙሉ በሙሉ ስለ ጨለመ በየአከባቢው ተቃዉሞ ማንሳትና የምርጫ ካርድ ከመውሰድ መታቀብ
የመሳሰሉ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ይገኛል። የስልጣን ዕድሜያቸው
እንዳያበቃ ስጋት ያደረባቸው የስርአቱ አስተዳዳሪዎች ግን አድማ በታኝ ብለው ያሰለጠንዋቸው ተላላኪዎቻቸው በመሰማራት ህዝቡን
እየጨፈጨፉ ከሰልፉ እየበተኑት ይገኛሉ።
ከዚህ በተጨማሪ
የምርጫ ካርድ ያልያዘ ሰው የህክምናና የፍትህ አገልግሎት እንዲሁም እንደ ሱኳር፤ ዘይትና ወዘተ… የመሳሰሉትን አታገኝም በማለት እያገዱት
ይገኛሉ።
ስለዚህ ለዚህ ሰላምን ለሚጠየፍ ፀረ ዴሞክራሲ ስርአት በሰለማዊ መንገድ ስልጣን
እንደማያስረክብ በግልፅ ቋንቋ ስለ ተናገረን ባመነበት የጠመንጃ ኣፈሙዝ ገጥመን ከስልጣኑ በመፈንገል በምትኩ በኢትዮጵያ ህዝብ ምሉ
ፍላጎት ይሁንታ የተመሰረተ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመምስረት የሚቻለው በመካሄድ ላይ ባለው ሁለገብ ትግል የድርሻችንን ለማድረግ ይቆይልኝ የማይባል ትክክለኛ እርምጃ
መሆኑን አምነን አሁን እንነሳ።