Saturday, December 29, 2012

በምእራብ ጎጃም በቡሬ ከተማ በአቶ ባንቲ በተባለ የኢህአደግ ካድሬ የተመራ የንግድ ማህበረሰብ ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ።

ከታሕሳስ 4/16/2005 ዓ/ም በተካሄደው ስብሰባ የተገኙት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ከቡሬ ከተማ ፤ ከፍኖተ ሰላም ፤ ከሰከላና ወንበርማ ወረዳዎች የተሰባሰቡ ሲሆን በስብሰባው የቀረቡ አጀንዳዎች  መልካም አስተዳደር እናስፈን ፤ ነጋዴው ፈጣን እድገት እንዲያስመዘግብ መደረግ ያለበት ጥረት በተመለከተ ሲሆን አጀንዳዎቹ ተቀባይነት አላገኙም  ተሰብሳቢዎቹ በማስከተል ቅድሚያ እንዲፈቱላቸው የሚፈሉጓቸውን ችግሮችን አቅርበዋል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት የኢህአደግ ስርዓት እውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በአገር ልማት በማዋል እራሳቸውን ፤ ወገናቸውንና አገራቸውን ለመጥቀም የሚንቀሳቀሱ ዜጎችን ህግና ደምብ በሚፈቅደው መሰረት አታስተናግዱም ቅድሚያ እምትጠይቁት ጉቦን ነው ፥ የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በስብሰባው በመነሳታቸው ስብሰባውን ሲመራ የነበረ ካድሬ በሁኔታው ተደናግጦ ከዓቅሜ በላይ ነው ሲል እንደገለጸላቸው ለማወቅ ተችለአል።
በስብሰባው ጥያቄ ካቀረቡ ነጋዴዎች መካከል አቶ ተሻለ ፤ አቶ ካሴና አቶ መሓሪ የተባሉ ይገኙባቸዋል፣  በወር 150 ብር ገቢ የሌለው ነጋዴ እንዴት በዓመት 150,000 ብር ግብር እንዲከፍል ይጠየቃል መንግስት የለም ወይ ? ሲሉም ጠይቀዋል።
ስብሰባውን እንዲመራ የተላከው ካድሬ የቀረቡትን ጥያቄዎች ከአቅሜ በላይ ስለሆኑ ምላሽ ለመስጠት ከክልል የሚመጣ ሰው መኖሩን ለተሰብሳቢዎች ከገለጸላቸው በሁዋላ በስብሰባው ከተገኙት 400 ነጋዴዎች መካከል ከ 30 በስተቀር የተረፉት ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።