Thursday, August 7, 2014

በአዲግራት ከተማ ለውሃ ልማት ተብሎ የተመደበ በጀት የፅህፈት ቤቱ ሓላፊ ልግል ጥቅሙ እያዋለው እንደሚገኝ ከአዲግራት ከተማ ምንጮቻችን ገለፁ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአዲግራት ከተማ ነዋሪ ህዝብ  በንፁህ የመጠጥ ውሓ እጥረት ምክንያት እየተሰቃየ ባለበት ሰዓት ለውሃ ልማት ተብሎ የተመደበውን በጀት መምህር ወላይ የተባለው የፅሕፈት ቤቱ ሓላፊ፣ ለውሃ ልማት ተብሎ የተመደበውን በጀት ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ በርካሽ ዋጋ እየገዛ አብዛኛውን ገንዘብ ለግሉ እያዋለው እንደሚገኝ መረጃው አስታውቋል።
    የሓላፊውን እኩይ ተግባር በመገንዘብ ትክክል አይደለም ብለው የተቃዎሙትን ሰራተኞች የከተማው የውሃ ልማት ፅ/ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ አካሄዱን ለተቃዎሙት ሰራተኞች ከተሰማሩበት የስራ መስክ እያባረራቸው እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣፣